Connect with us

አማርኛ

አቶ ጌታቸው ረዳ አዲስ አበባ ከሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ጋር ተወያዩ

Kulu Media

Published

on

የትግራይ ህዝብ የፕሪቶሪያ ስምምነት የሰጠውን ወርቃማ ዕድል በመጠቀም ሰላሙን ማፅናት እንደሚገባው የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ገለጹ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ውይይት እያደረጉ ይገኛሉ::

በውይይቱም የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ተገኝተዋል::

አቶ ጌታቸው ረዳ የፕሪቶሪያ ስምምነት የትግራይ ህዝብ ለዓመታት የተጠማውን ሰላም እንዲያገኝ በማድረግ ረገድ ውጤት የተገኘበት ነው ብለዋል። አክለውም የተቋረጡ መሰረተ ልማቶችን ዳግም ወደ ስራ እንዲገቡ ከማድረግ ጀምሮ ሰላምን በማፅናት በኩልም ጠንካራ ስራ ተሰርቷል ብለዋል::

ይሁን እንጂ በህወሓት አመራሮች መካከል በነበረው ፖለቲካዊ መሳሳብ ምክንያት በስምምነቱ መሰረት እንዲፈፀሙ የተቀመጡ ጉዳዮች የራስን የግል ጥቅም ብቻ በማስቀደም ሊሳኩ አለመቻላቸውን አንስተዋል::

በክልሉ ህዝብ ዘንድ ትኩረት ከሚሹ ጉዳዮች መካከል አንዱ የተፈናቃዮች ሁኔታ ነበር ያሉት አቶ ጌታቸው፣ ይህንን ጥያቄ ግን የህወሓት ቡድን ትኩረት በመንፈግ ከሰብአዊነት ይልቅ የራሱን ፖለቲካዊ ፍላጎት ብቻ ለማሳካት ሲል ተጠቅሞበታል ብለዋል::

ዛሬም ቢሆን ቡድኑ የትግራይ መሬትን ዳግም የጦርነት አውድማ ከማድረግ ውጪ አላማ የለውም ያሉት አቶ ጌታቸው፣ የትግራይ ህዝብ የፕሪቶሪያ ስምምነት የሰጠውን ወርቃማ ዕድል በመጠቀም ይህንን እኩይ ተግባር ሊቃወም እና ሰላሙን ማፅናት እንደሚገባው ተናግረዋል::

በመድረኩም የተሳተፉ በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆችም የተለያዩ ጥያቄዎችን እያነሱ ሲሆን፣ ከመድረክ ምላሽ እና ማብራሪያ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል:: ሲል አዲስ ሚድያ ኔትዎርክ ዘግበዋል።

ስዓቡና

YouTube

Facebook

TikTok

Instagram


Discover more from Kulu Media ኩሉ ሚድያ

Subscribe to get the latest posts sent to your email.

Discover more from Kulu Media ኩሉ ሚድያ

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading